አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ
- BETE YARED
- Jul 23, 2021
- 2 min read
Updated: Jun 22, 2022
July 22, 2021
አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ ኢትዮጵያዊዉ ፃድቅ ረድኤት በረከት አይለየን!!! አቡነ እስትንፋስ ክርስቶስ የስማቸው ትርጓሜ የክርስቶስ፣ የአብ ፣ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስ ማለት ነው ፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፊታቸው ላይ እፍ ብሎ ጸጋውን፣ በረከቱን ስላሳደረባቸው በዚህ ስም ይጠራሉ ፡፡ የጻድቁ፣ የአባታቸው ስም መልአከ ምክሩ ሲሆን ፤ የእናታቸው ወለተ ማርያም ይባላሉ ፡፡ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ፃድቅየተወለድት በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ዳውንት ዐወን ዓባይየአባት ስምመልአከ ምክሩየእናት ስምወለተ ማርያምየትውልድ ዘመንታኅሣሥ ፰ ቀንበዓለ ንግሣቸውባረፉበት ሚያዚያ ፱ ቀንየሚከበሩትበመላው የኢትዮጵያ ርትዕት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በተለይ በዳውንት ከተማ ደብረ አስጋጅ ገዳም የትውልድ ቦታቸው በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ዳውንት ዐወን ዓባይ የተባለ አካባቢ ነው ፡፡ የተፀነሱት ሚያዝያ ፰፤ የተወለዱት ደግሞ ታኅሣሥ ፰ ቀን ነው ፡፡ የሕይወት ታሪካቸው ተጋድሎዋቸውና ታመራቸው አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ፣ ዐቢይ ጾምን ዐርባ ሌሊትና ዐርባ ቀን እኽልን ውኃ ሳይቀምሱ ይጾሙ ነበር፡፡ እግሮቻቸው እስኪያብጡ ድረስ ቆመው ይጸልዩ ነበር፡፡ ለሽፋሽፍቶቻቸውም ዕረፍትን አይሰጡአቸውም ነበር፡፡ በአንድ ወቅት ወደ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ገዳም ሲሔዱ ወደ ገዳሙ ለመግባት ሐይቁን የሚያሻግራቸው ቢያጡ ተንበርክከው ሲጸልዩ በቅዱስ ሚካኤል እጅ ደንገል (ታንኳ) ቀርቦላቸው ሐይቁን ተሻግረዋል፡፡ ዘጠኝ ዓመት ዓባይ ባሕር ውስጥ በራሳቸው ተዘቅዝቀው በመቆም ለኢትዮጵያ ሲጸልዩ ከቆዩ በኋላ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እርሳቸው መጥቶ ‹‹ከመነኮሳት ዂሉ ብልጫ ያለህ ወዳጄ እስትንፋሰ ክርስቶስ ሆይ፥ ኢትዮጵያን ምሬልሃለሁና ከዚህ ባሕር ውጣ›› ብሏቸዋል፡፡ ከዚያም ማረፊያቸው ወደ ኾነች ዳውንት (ደብረ አስጋጅ) በመመለስ ዐሥራ ሰባት ገዳማትን መሥርተዋል፡፡ ወደ ደብረ ዳሞ በሔዱ ጊዜም በትእምርተ መስቀል አማትበው ያለ ገመድ ከደብረ ዳሞ ተራራ ላይ በመውጣት ከአቡነ አረጋዊ ጋር (ከተሰወሩበት ቦት መጥተው) ተገናኝተዋል፡፡ በየገዳማቱ ሲዘዋወሩ ከሞላ ውኃ በደረሱ ጊዜ በመስቀል ምልክት አማትበው በእግራቸው እንደ ደረቅ መሬት እየረገጡ ይሻገሩ ነበር፡፡ አምስት አንበሶችና አምስት ነብሮች ይከተሏቸው ነበር፤ እነዚያም አንበሶችና ነብሮች የሚመገቡትን ባጡ ጊዜ ድንጋዩን ባርከው ሥጋ ያደረጉላቸው ነበር እነሱም ያንን ይመገቡ ነበር፡፡ የትግራይን አድባራትና ገዳማትን ለመጐብኘት ወደ ቅዱስ ያሬድ ደብር ሲደርሱ እመቤታችን ከቅዱስ ያሬድ (ከብሔረ ሕያዋን መጥቶ) እና ከልጅዋ ጋር ወደ እርሳቸው መጥታ ብዙ ተአምራትን አድርጋላቸዋለች፤ ከቅዱስ ያሬድም ተምረዋል፤ ቡራኬ ተቀብለዋል፡ #ከተቀበሉት_ቃልኪዳን አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ከጌታችን ከመድኀኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ከተቀበሉት ቃል ኪዳን ጥቂቱ ዝክራቸውን የዘከረ፣ መታሰቢያቸውን ያደረገ፣ ስማቸውን የጠራ፣ ገድላቸውን የጻፈ፣ ያጻፈ፣ ያነበበ፣ የተረጐመ፣ የሰማ፤ በፍጹም ልቡና ‹‹አምላከ እስትንፋሰ ክርስቶስ (የእስትንፋሰ ክርስቶስ አምላክ) ኀጢአቴን ይቅር በለኝ›› ብሎ የጸለየ ስሙ በሕይወት መጽሐፍ ይጻፍለታል፡፡ ለቤተ ክርስቲያናቸው መባዕ፣ ስንዴ፣ ዘይት፣ ዕጣን፣ ጧፍ የሰጠ ኀጢአቱ ይደመሰስለታል፤ በገነት፣ በመንግሥተ ሰማያት በደስታ ይኖራል፡፡ በስማቸው የተራቆተውን ያለበሰ፣ የተራበውን ያበላ፣ ያዘነውን ያረጋጋ፣ በመታሰበያቸው ዕለት ለአገልግሎት የሚፈለገውን መልካሙን ነገር ያደረገ ኀጢአቱ ይሰረይለታል፡፡ በየዓመቱ ሚያዚያ ፱ ቀን እና በየወሩ የዕረፍታቸውን መታሰቢያ በዓል ያከበረ፣ ዝክራቸውን የዘከረ ሰማያዊ ክብር ያገኛል፡፡ በስማቸው የጽዋ ማኅበር የሚጠጡ ሰዎች ቢኖሩ በመካከላቸው የጻድቁ አምላክ ይገኛል፡፡ ዝክራቸውን የዘከሩ፣ መታሰቢያቸውን ያደረጉ፣ በስማቸው የተማጸኑ፣ በገድላቸው የተሻሹ፣ በጠበላቸው የተጠመቁና የጠጡ መካኖች ልጅ ይወልዳሉ፡፡ ችግር ደርሶበት ስማቸውን የጠራ፣ ወንድ ወይም ሴት ልጁን በስማቸው የሰየመ፣ በበዓላቸው ቀን ቁራሽ እንጀራና ቀዝቃዛ ውኃ ለነዳያን የሰጠ ኀጢአቱ ይሰረይለታል ፡፡ የአባታችን የአቡነ እስትንፋስ ክርስቶስ ረድኤት በረከታቸው ጸሎት ልመናቸው በያለንበት አይለየን አሜን!!! አሜን!!! አሜን!!!
Comentários