top of page
ethiopiancross.png

ጥቂት ስለ ቤተ ክርስቲያናችን

ራዕይ

ሁሉን አቀፍ መንፈሳዊ አገልግሎት የቤተክርሲቲያንን መወቅርና አሰራር ተከትሎ በሚጠበቀው መንገድ ማከናወንና የመልካም አስተዳደርን ባህል በማሳደግ ትክክለኛ የሆነ የመንፈስ ልዕልና ያለው ምእመንና የኢኮኖሚ አቅሟ የተሟላ ቤተክርስቲያንን መገንባት።

ተልዕኮ

ዓላማና  ግብ

ዓላማ

  • የእግዚአብሔርን ቃል ለምእመናን በተለያየ መንገድ በማዳረስ ጠንካራ መንፈሳዊ ሕይወት ያለው ምእመን መፍጠር፥ 

  • የራስ የሆነ የአምልኮት ቦታ መመሰረት እና የቤተክርስቲያናችንን መንፈሳዊ አገልግሎት አድማስ ማስፋፋት
     

ግብ

  • የቤተክርስቲያንን ስርዓት በማስተማርና ወንጌልን በመስበክ ጠንካራና ደረጃውን የጠበቀ መንፈሳዊ ሕይወት ያለው ምእመን መፍጠር፡፡ የፈቃድ አገልግሎትን በስፋት በቤተክርስቲያን በማጠናከር  የቤተክርሲቲያን ገቢ ማሳደግና የአገልጋዮቹ ካህናት ህይወት በተገቢው መንገድ መደገፍ፡፡

መልዕክት ከተጋባዥ ካህን

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

ውድ የቤተክርስቲያናችን አባላት፥

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጥንታዊት፥ታሪካዊት፥ሐዋርያዊት የሆነች ስትሆን መስራችዋም ጌታችን መድyኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ፡፡ በመሆኑም ይህ ማንነትዋ በአፍሪካም ሆነ በመላው የክርስትና ዓለም ልዩ ገÎታና ቦታ ያላት አድርጓታል፡፡ ቤተክርስቲያኗ ከመንፈሳዊ አገልግሎቷ ባሻገር ለተከታዮቿ መንፍሳዊና ማሕበራዊ ልዕልና ትልቅ አስተዋጽኦ አላት። 

ቤተክርስቲያናችሁ የእናንተን ዱካ እየተከተለች በምትኖሩበት ሁሉ በአገርም ሆነ በውጭው ዓለም እየተከተለች የሚያስፈልጋችሁን መንፈሳዊ አገልግሎት እየሰጠች ትገኛለች። ስለዚህም ነው አሁንም እናንተ በምትኖሩበት አገር በፒትስበርግ የተቋቋመችው። የቤተክርስቲያንዋ የረጅም ዘመን ጥንታዊ ታሪካዊና ሐዋርያ እሴቶት ለአዲሱ ትውልድ መተላለፍ አለበት። ይህን ሃሳብ ደግሞ ተግባራዊ ለማድረግ ይህ ዌብ ሳይት ለቤተክርስቲያን አባላት፤ፍላጎት ላላቸው ቡድኖችና ቱሪስቶች የተቀናጀ መረጃ በማቅረብ በኩል ትልቅ ሚና ይኖረዋል። በመሆኑም እኔ በይሁዳ መልዕክት ቀጥሎ እንደተጠቀሰው በሃይማኖታችሁ ጠንካራ እንድትሆኑ አሳስባለሁ። “ወዳጆች ሆይ፥ ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ፥ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ::” ይሁዳ 1፡3

የእግዚአብሔር ሰላምና ፍቅር ከሁላችሁ ጋር ይሁን!!!

ቀሲስ ዶር ሙሉጌታ ስዩም

የቤተ ክርስቲያን ዋና ተልኮዋ የእግዚአብሔርን ቃል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደተናገረው በመላው ዓለም መስበክ ነው። “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።” ማቴ 28:19

ከላይ በተቀመጠው ተልዕኮ መሰረት ቤተከርስቲያን የሚከተሉት ታከናውናለች:

  • ምእመናን እምነታቸውን ትውፊታቸውንና   እሴቶቻቸውን እንዲያውቁና እንዲጠብቁ ታደርጋለች

  • የቤተክርስቲያን የሃይማኖትና የስነምግባር ትምህርቶች እንዲስፋፉ ማድረግ

  • የቤተክርስቲያን ሀብትና ንብረት ለታለመለት ስራና ዓላማ በቤተክርስቲያን ሕግና ስርዓት መሰረት እንዲውል ማድረግ

  • በፒተስበርግ ከተማ የሚገኙ ኢ አማንያን ተምረው የቤተክርስቲኣን አባል የሚሆኑበትን አገልግሎት ማከናወን

  • ቤተ ክርስቲያን በተመሰረተችበት አገር ካላት ታሪካዊና ማህበራዊ እሴቶች አንጣር በሚኖረው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ የጎላ ተሳትፎ እንዲኖራት ማድረግ

  • የካህናትን መብትና ግዴታ በተገቢው መንገድ እውን ማድረግ

  • ምእመናን ቤተክርስቲያናቸውን በእውቀታቸው በጉልበታቸውና በገንዘባቸው እንዲያገለግሉ አስፈላጊውን ምቹ ሁኔታ መፍጠር 

  • በጥሩ አእምሮና ስነምግባር የተገነባ ውጤታማ ሕይወት ያለው ምእመን መፍጠር

  • የሰንበት ትምህርት ቤትን በማጠናከር ወጣቱንና ሕጣናቱ በመንፈሳዊ ሕይወታቸውና በማህበራዊ ሕይወታቸው የተሻሉ እንዲሆኑ ማድረግ

  • Facebook
  • Twitter
  • Instagram
bottom of page